የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የቀን ለውጥ ተደረገበት

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የ2012 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር የቀን ለውጥን ተደርጎበታል፡፡

የሁለቱ ውድድሮች የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ቀድም ብሎ ቅዳሜ ህዳር 13 ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በአንድ ሳምንት ተገፍቶ ህዳር 20 እንዲከወን መደረጉ ታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ የዕጣ ማውጣቱ ቀን ላይ ለውጥ ቢያደርግም በውድድር ዘመኑ መጀመርያ ቀን ላይ ለውጥ ስለማድረግ አለማድረጉ ያለው ነገር የለም። የአንደኛ ዲቪዝዮኑ ውድድር ኅዳር 27፣ የሁለተኛ ዲቪዝዮኑ ደግሞ ታኅሳስ 18 እንዲጀመር መወሰኑ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ