የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ | ተጠባቂውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቋል

ምዓም አናብስት እና ዐፄዎቹ የሚያደርጉት ተጠባቂው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታን የሚዳኙት አራት ዳኞች ተለይተዋል።

በነገው ዕለት የሚደረገው ይህ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታን በዋና ዳኝነት በላይ ታደሰ፣ በረዳት ዳኝነት ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው እንዲሁም ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኝነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ከዚህ ቀደም ጥቅምት 23 እንዲካሄድ ተወስኖ ሁለቱም ቡድኖች አዲስ አበባ ላይ ልምምድ ከጀመሩ በኋላ በፀጥታ ምክንያት የተራዘመው ይህ ጨዋታ ነገ ኅዳር 16 እንዲካሄድ ባሳለፍነው ሳምንት መወሰኑ ይታወቃል።

ባለፈው ዓመት በሊጉ ላይ የቅርብ ተፎካካሪዎች የነበሩት ሁለቱ ቡድኖችን የሚያገናኘው ይህ ጨዋታ በሜዳ ላይ ከሚታየው አጓጊ ፉክክር በተጨማሪ ከሜዳ ውጭ ባሉት በርካታ ጉዳዮች ምክንያት ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ