ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሴካፋ ዋንጫ ይሳተፉ ይሆን?

በዩጋንዳ አዘጋጅነት በሚካሄደው ሴካፋ ዋንጫ ላይ በአንድ ምድብ የተደለደሉት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የመካፈላቸው ጉዳይ ቁርጡ አለየለትም።

ለውትሮው እንከን የማያጣው የሴካፋ ሀገራት ዋንጫ ባሳለፍነው እሁች በታንዛኒያ ዳሬሰላም በሦስት ምድብ የተከፈለ ድልድል ይፋ በማድረግ ከሳምንት በኃላ ውድድሩን ለመጀመር መታቀዱ ይታወቃል። ከዩጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ከኤርትራ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ጥረት እያደረገች ይገኛል። በተለይ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በወጣት የተገነባ ሁለተኛ ብሔራዊ ቡድን ለመስራት በውድድሩ ላይ ለመካፈል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ተናግረዋል።

ሆኖም ፌዴሬሽኑ ካለበት የፋይናስ እጥረት አንፃር ላይሳተፉ እንደሚችሉ እና መንግስት (የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን) ለብሔራዊ ቡድኑ ጉዞ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛል። ጥረቱ ተሳክቶ ስፖርት ኮሚሽን መልካም ትብብሩ ከሆነ ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ልትሳተፍ የምትችልበት እንድል እንደሚኖር ሰምተናል።

በሌላ ዜና የምድብ ጨዋታ ተጋሪዋ ኤርትራ በዚህ ውድድር ላይ ላትሳተፍ እንደምትችል እየተነገረ ይገኛል። በተደጋጋሚ ከሀገሯ ውጭ በሚደረጉ ውድድሮች ተጫዋቾች እየጠፉ የሚገኝባት ኤርትራ በዚህም ውድድር ላይ ተጫዋቾቿ እንዳይጠፉ በመስጋት ይመስላል ላለመካፈል እያሰበች እንደሆነ የተሰማው።

በአንድ ምድብ መደልደላቸውን ተከትሎ ከሁል አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ጨዋታ ለማድረግ አጋጣሚ የተፈጠረላቸው ሁለቱ አገራት አለመሳተፍ ዕውን ከሆነ ውድድሩን እንዳይደበዝዘው ተሰግቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ