ኢትዮጵያ በሴካፋ ዋንጫ አትሳተፍም

ከቀናት በኃላ በሚካሄደው የዘንድሮው የሴካፋ ዋንጫ እንደማይሳተፍ ተገምቶ የነበረ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ ተረጋግጧል።

ከቀናት በኃላ በሚጀምረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በምድብ አንድ ከዩጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ኤርትራ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ካጋጠማት የገንዘብ እጥረት አኳያ ፌዴሬሽኑ መንግስት ድጋፍ እንዲደረግለት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ከዚህ ቀደም መግለፃችን ይታወቃል።

ሆኖም ጥረቱ ሳይሳካ በመቅረቱ ኢትዮጵያ ከሴካፋ ዋንጫ ዘንድሮ እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል። ትናንት የምድብ ጨዋታዎቹ ቀን እና ሰዓት ይፋ በተደረገበት የሴካፋ ውድድር በብዙዎች ተጠብቆ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታም አለመካሄዱ እርግጥ ሆኗል።

በሌላ ዜና ኤርትራ በዚህ በሴካፋ ዋንጫ ውድድር ላይ እንደማትሳተፍ እየተነገረ ቢሆንም እስካሁን የመሳተፉ አለመሳተፏ ጉዳይ ቁርጡ አለየለትም።


© ሶከር ኢትዮጵያ