የ2012 ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበት ቀን ተራዘመ

በሦስት ምድብ ተከፍሎ በ36 ክለቦች መካካል የሚካሄደው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚካሄድበት ቀን ተራዝሟል።

አስቀድሞ እሁድ ኀዳር 27 ቀን እንደሚጀመር የተገለፀ ቢሆንም የ2012 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዓመታዊ ውድድር አስመልክቶ በጁፒተር ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ ስብሰባ እና የምድብ ድልድል ሥነ ስርዓት ላይ ክለቦች ውድድሩ እንዲራዘም ጥያቄ አቅርበዋል።

በዚህ መሠረት የክለቦቹ ጥያቄን አዲሱ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ በአንድ ሳምንት ወደ ፊት ገፍቶ ቅዳሜ ታኀሳስ 4 እና 5 ቀን እንዲጀምር ወስኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ