ኹለት የዚህ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደረገባቸው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኹለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሲቀጥሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሰበታ ከተማ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከጅማ አባጅፋር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደርጎባቸዋል፡፡

አስቀድሞ በወጣው የኹለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መሠረት ስድስት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ ኹለት ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ ይደረጋሉ ተብሎ ቢጠበቅም የብሔር ብሔረሰቦች በዐል የፊታችን ሰኞ የሚከበር በመሆኑ በአዲስ አበባ ሊደረጉ የነበሩ ኹለት ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደርጎባቸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዳሜ በ9:00 ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከተማ ጨዋታ ማክሰኞ ኅዳር 30 በ11:00 እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን በተመሳሳይ ዕሁድ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ ደግሞ ረቡዕ ታህሳስ 1 በ11:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲጫወቱ አዲሱ የውድድር እና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ ረፋድ ባደረገው ስብሰባ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ