የካፍ ፕሬዝደንት ኢትዮጵያ ይገኛሉ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዘደንት አህመድ አህመድ ለስራዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

አዲሱ የካፍ ፕሬዝደንት ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ አንስቶ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አህመድ አህመድ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ይገኛሉ። አብረዋቸው በመሆንም የፊፋ ዋና ጸሐፊ ፈጡማ ሳሞራ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።


ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር እንደሚነጋገሩ ሲጠበቅ በተጨማሪም የግንባታው የመጀመርያ ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ግንባታ ያመራው አዲሱን የአደይ አበባ ስታድየምን እንደሚጎኙ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ