የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ አዳማ ከነማ በሜዳው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አስተናግዶ 1-1 ከተለያየ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች እንደሚከተለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ተጫዋቾቼ ዛሬ ላሳዩት ትጋት አመሰግናቸዋለው” ሳሙኤል አበራ – አዳማ ከተማ

ስለ ጨዋታው

እንደ መጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ጥሩ ነው። ተጋጣሚያችን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠንካራ ተፎካካሪያችን ከመሆኑ አንፃር ቡድኔ በዛሬው ጨዋታ በኳስ ቁጥጥሩ የተሻለ ነበር። ሆኖም የግብ ክልል ውስጥ የአጨራረስ ችግር ታይቶብናል። ይህንም በሚቀጥለው ጊዜያት የምናስተካካል ይሆናል። የተጋጣሚያችን ሜዳ ክፍል ላይ መጫወት ብንችልም ፊት ላይ ግን ችግሮች ታይተዋል። በሚቀጥለው የምናስተካክለው ይሆናል።

ግቧ የተቆጠረችበት ሂደት

ውሳኔው የዳኛ ቢሆንም በእኔ እይታ ሽታዬ ከጨዋታ ውጪ ነበረች። ኳሱን ስተቀበል ከጨዋታ ውጪ መሆን መቻል ነበረባት። የኔም ተጫዋቾች ይህን አስበው ነበር የተዘናጉት። ተከላካዩ ናርዶስ ሮጣ ለማዳን ብትሞክርም አልተሳካም። ናርዶስም ሆነች ሴናፍ ከነ ህመማቸው ነበር የተሰለፉት። ባጠቀላይ ግን ተጫዋቾቼ ዛሬ ላሳዩት ትጋት አመሰግናቸዋለው።

“በውጤቱ ደስተኛ ነኝ” ብርሃኑ ግዛው – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታ ስናደርግ እንግዲህ ከብዙ ወራቶች በኋላ ነው። ዛሬ የገጠምነው ቡድን ደግሞ የዐምናው ሻምፒዮን አዳማን ነው። ስንመጣም ኳስ ይዘው እንደሚጫወቱ እናውቅ ነበር። ለዛ የሚሆን አጫወት ይዘን ነው የመጣነው። ባስመዝገብነው ውጤት እንደኔ ደስተኛ ነኝ። ከሜዳ ውጭ ስትጫወት ከባዱ ነገር ሶስት ነጥብ ማሳካት ነው። ዛሬ ላይ ያለብንን ክፍተት በደንብ አይተንበታል፤ ለሚቀጥለው አስተካክለን እንመጣለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: