አራት የስሑል ሽረ ተጫዋቾች በቀጣይ እሁዱ ጨዋታ ቡድናቸው አያገለግሉም

አራት የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ልምምድ አቁመው ከቡድኑ ጋር አልተጓዙም።

ተጫዋቾቹ ክለባችን ቀደም ብሎ ቃል በገባልን መሰረት ደሞዛችን በጊዜው መክፈል አልቻለም በሚል በፈቃዳቸው ልምምድ በማቆም ነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሚገጥመው ስብስብ ውጭ የሆኑት። ሳሊፍ ፎፋና፣ ያሳር ሙገርዋ፣ ዲድዬ ለብሪ እና አክሊሉ ዋለልኝ ልምምድ ያቆሙት ተጫዋቾች ሲሆኑ ያልተከፈላቸው ደሞዝ ከሦስተኛው ሳምንት በፊት ይከፈላችኋል ተብሎ የተገባላቸው ቃል እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልቻለ ከታማጭ ምንጮች ሰምተናል።

በዚህም መሠረት በፋይናንስ እጥረት እየተቸገሩ የሚገኙት እና ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈው በቀጣይ መርሐግብር ከሜዳቸው ውጪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥሙት ስሑል ሽረዎች በቀጣዩ ጨዋታ የአራቱም ተጫዋቾች ግልጋሎት አያገኙም።


© ሶከር ኢትዮጵያ