ኮከቦቹ ሽልማታቸውን አልተቀበሉም

የኮከቦች ሽልማት በጊዜው አለመጠናቀቅ ቅሬታ እያስነሳ ነው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ታኅሣሥ 27 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በ2011 በተካሄዱ ውድድሮች ኮከኮች ላላቸው አካላት ሽልማት ማበርከቱ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ባለፉት ሁለት ዓመታት የዚህን ሽልማት ክፍያ በግዜው መክፈል ያልቻለው ፌደሬሽኑ ዘንድሮም በተመሳሳይ ለኮከቦቹ ሽልማቱ ሳይሰጣቸው ወራቶች ተቆጥረዋል።

በወንዶች ዘርፍ ከአንደኛ ሊግ እስከ ፕሪምየር ሊግ በሴቶች ዘርፍ ደግሞ በፕሪምየር ሊግ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፣ ኮከብ አሰልጣኝ እና ምስጉን ዳኞች ሽልማት የነበረው ይህ የሊጉ ትልቅ ሽልማት ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ችግሮች ማስተናገዱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ