ለ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 23 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከዚምባብዌ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ እንደተደረገላቸው ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መጋቢት 13 የሚያደርግ ሲሆን ለዚህ ጨዋታም 23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ከሰኞ ጀምሮም ዝግጅት እእደሚጀምሩ ታውቋል።

የተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች (2)፡ ዓባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)

ተከላካዮች (8)፡ ታሪኳ ደቢሶ (ኢት/ን/ባንክ)፣ ብርቄ አማረ (አቃቂ ቃሊቲ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢት/ን/ባንክ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት ፀጋዬ (አዳማ ከተማ)፣ ምሕረት መለሰ (መከላከያ)፣ ትዕግስት ኃይሌ (ኤሌክትሪክ)፣ ቤቲ በቀለ (ጌዴኦ ዲላ)

አማካዮች (6)፡ እመቤት አዲሱ (ኢት/ን/ባንክ)፣ አረጋሽ ካልሳ (መከላከያ)፣ ገነት ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ ሲሳይ ገብረዋህድ (መከላከያ)፣ ቤተልሄም ዘውዱ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ መሳይ ተመስገን (ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች (7)፡ አርያት ኦዶንግ (ኢ/ወ/ስ አካዳሚ)፣ ረድኤት አስረሳኸኝ (ጌዴኦ ዲላ)፣ ምርቃት ፈለቀ (አዳማ ከተማ)፣ የምስራች ላቀው (አዳማ ከተማ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (መቐለ 70 እንደርታ)፣ ሥራ ይርዳው (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ)

© ሶከር ኢትዮጵያ