እንዳለ ከበደ ስድስተኛ የድሬዳዋ ከተማ ፈራሚ ሆኗል

የመስመር ተጫዋቹ እንዳለ ከበደ ማረፊያው የምስራቁ ክለብ ሆኗል፡፡

ከቀናት በፊት የስድስት ወራት ውል እየቀረው ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በስምምነት የተለያየው እንዳለ ከበደ ከዚህ ቀደም ወደ ድሬዳዋ ለማምራት ጫፍ መድረሱን ዘግበን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ዝውውሩን በማጠናቀቅ ስድስተኛ አዲስ ፈራሚ ሆኖ ብርቱካናማዎቹን ተቀላቅሏል።

ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እና መቐለ የተጫወተው እንዳለ በጉዳት እየተቸገረ በሚገኘው የድሬዳዋ ስብስብ ጥሩ የመስመር አማራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ድሬዳዋ በዚህ የዝውውር መስኮት ከእንዳለ ቀደም ብሎ ሄኖክ ኢሳይያስ፣ ክዌክ አንዶህ፣ ኑሁ ፉሴይኒ፣ ምንያምር ጴጥሮስ እና ይስሀቅ መኩርያን አስፈርሟል።

© ሶከር ኢትዮጵያ