ያሬድ ሀሰን እና ድሬዳዋ ተለያዩ

የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ሀሰን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

የቀድሞው የወልዲያ ተጫዋች በ2010 ክረምት መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ ዐምና ከቡድኑ ጋር ዋንጫ ያሳካ ሲሆን ዘንድሮ በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ክለቡን በመልቀቅ ብርቱካናማዎቹን በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ክለቡን እምብዛም ማገልገል ያልቻለው ይህ ተጫዋች የስድስት ወራት ውል እየቀረው በስምምነት ድሬዳዋን የለቀቀ አራተኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡

እስከ አሁን ስድስት ተጫዋቾችን በአዲስ መልክ ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ በቀጣዮቹ ቀናት አንድ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ለማስፈረም በሒደት ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ