ወልቂጤ ከተማ የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር የተለያየው ኢዩኤል ሳሙኤል የወልቂጤ ሶስተኛ ፈራሚ ሆኗል።

እዮኤል ሳሙኤል ሆሳዕና ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የፊት መስመሩን በመምራት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ ቢሆንም ዘንድሮ በሊጉ የተጠበቀውን ያህል የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱን ተከትሎ ከክለቡ ጋር በመለያየት ወደ ወልቂጤ ማምራት ችሏል።

የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ እና ድሬዳዋ ፖሊስ ተጫዋች በወልቂጤ በቅርቡ ቡድኑን የለቀቀው ሄኖክ አወቀን ቦታ የሚሸፍን ሲሆን ለቡድኑ የመስመር እንቅስቃሴ ተጨማሪ ኃይል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ