መቐለ 70 እንደርታ ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

በክረምቱ የኢራቁን ክለብ አል ካርባላ ለቆ መቐለ 70 እንደርታን የተቀላቀለው ላውረንስ ኤድዋርድ አግቦር በስምምነት እንደተለያየ ክለቡ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ለካርባያ፣ አልሲናት እና ለቱኒዚያው ኤትዋል ዱ ሳህል መጫወት የቻለው ይህ ግዙፍ ተከላካይ በመጀመርያዎቹ የሊግ ጨዋታዎች በቋሚነት ክለቡን ቢያገለግልም ቆይቶ የአሰልጣኙ ሁለተኛ ምርጫ ሆኗል። መቐለን ከተቀላቀለ በኃላ በዘጠኝ ጨዋታዎች በቋሚነት ጀምሮ 896 ደቂቃዎች የተጫወተው ይህ ናይጀርያዊ ተከላካይ በውድድር ዓመቱ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።

ተከላካዩ ጋር የተለያዩት መቐለዎች ባለፈው ሳምንት ባስፈረሙት በተስፋዬ በቀለ ቦታውን እንደሚሸፍኑ ሲጠበቅ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ እንደሚወጡም ለማወቅ ተችሏል።

©ሶከር ኢትዮጵያ