አክሊሉ አየነው በይፋ ወልዋሎን ተቀላቅሏል

ላለፉት ቀናት ከወልዋሎ ጋር ልምምድ እያደረገ የቆየው ተከላካዩ አክሊሉ አየነው ዛሬ ፊርማውን አኑሯል።

ከዚ ቀደም ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ቡናና ደደቢት መጫወት የቻለው ይህ ተከላካይ በጉዳት እና አቋም መውረድ ለታመሰው የወልዋሎ የተከላካይ ክፍል ጥሩ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።

ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ውጤታቸውን አስጠብቀው የመውጣት ክፍተት የታየባሸው ወልዋሎዎች በአዲሱ አሰልጣኝ ስር ተጨማሪ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላ ከወልዋሎ ጋር የተያያዘ ዜና የክለቡ ደጋፊዎች በወቅታዊ ጉዳት ላይ ከተጫዋቾቹ እና ከክለቡ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

©ሶከር ኢትዮጵያ