ሀዋሳ ከተማ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሾመ

ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ዘሪሁንን የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በማድረግ ቀጥሯል፡፡

የረጅም ዓመት የክለቡን አምበል እና ተጫዋች የነበረውን ሙሉጌታ ምህረትን በቅርቡ ሀይቆቹ በዋና አሰልጣኝነት መንበር ለአንድ ዓመት ከግማሽ ወራት ቆይታ መቅጠራቸው ይታወሳል፡፡ አሰልጣኙም ከተቀጠረ በኃላ ከዚህ ቀደም አብሮት የተጫወተው እና የተስፋ ቡድን አሰልጣኝ የነበረውን ብርሀኑ ወርቁ (ፈየራ) ሁለተኛ ረዳት አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡ ይታወሳል፡፡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ፍለጋ ላይ የቆየው ክለቡም ወጣቱን አሰልጣኝ ቅዱስ ዘሪሁንን የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በማድረግ በአንድ አመት የውል ኮንትራት መሾሙን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

በተጫዋችነት ዘመኑ ለደቡብ ፖሊስ፣ ለባቱ ከተማ፣ አርሲ ነገሌን ለመሳሰሉ ክለቦች ከዚህ ቀደም የተጫወተው አሰልጣኝ ቅዱስ እግር ኳስን ካቆመ በኋላ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ የታዳጊ ህፃናትን ከማሰልጠን አንስቶ ወጣት ታዳጊ ቡድኖችን በወሰደው የሲ ላይሰንስ እና የግብ ጠባቂ የአሰልጣኝነት ስልጠና መሠረት ረዘም ላለ ዓመት እያሰለጠነ በርካታ ተጫዋቾችን አፍርቷል ፡፡ አሰልጣኙ ከዚህም በተጨማሪ የደቡብ ክልል የእግርኳስ ቡድኖችን በተለያየ ወቅት በዋና አሰልጣኝነት የመራ ሲሆን በያዝነው አመት ተሰናባቹን አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን ያለምንም ኮንትራት በቅርብ ርቀት ሲያገለግል ከቆየ በኃላ ነው በይፋ የተሾመው፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ