የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ጥያቄ እና የክለቡ ምላሽ

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች የደሞዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ክለቡም ምላሹን ሰጥቷል።

ከቀናት በፊት በቁጥር ጥቂት የማይባሉ የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ክለባቸው ደሞዛቸው እንዳልከፈላቸው እና በችግር ውስጥ እንዳሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀው ነበር። እንደ ተጫዋቾቹ ሀሳብ ክለቡ ያልከፈላቸው ደሞዝ እንዳለ እና። ከወቅታዊ የወረርሺኙ ሁኔታ ጋር ተደማምሮ ችግር ውስጥ እንዳሉ ገልፀው ክለቡ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ ምላሻቸው የሰጡት የስሑል ሽረ ስራ አስከያጅ አቶ ተስፋይ ዓለም የተጫዋቾቹ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አምነው ለክለቡ በይፋ የደሞዝ ጥያቄ ያቀረበ ተጫዋች እንደሌለ ግን ገልፀዋል። ” ትክክል ነው፤ አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር የፋይናንስ ችግር አለብን። ይህንን ችግር ለመፍታትም እንቅስቃሴ ጀምረናል። ካለን የፋይናንስ ችግር አንፃር በጉዳዩ ላይ ከተጫዋቾቻችን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነን። ሆኖም ስለ ደሞዝ ጥያቄ እና ተያያዥ ጥያቄዎች በይፋ የጠየቀን ተጫዋች የለም፤ ጥያቄ ካቀረቡ ግን አንዳንድ ክለቦች እንዳደረጉት በመፍትሔ ሃሳቦች ላይ በቅርበት ለመወያየት ዝግጁ ነን።” ብለዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ