ፋሲል ከነማ አዲስ ተጫዋች ሲያስፈርም የነባሮችን ውል አድሷል

ዐፄዎቹ የባህርዳር ከተማውን ግርማ ዲሳሳን ሲያስፈርሙ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል በአንፃሩ አራዝሟል፡፡

ክለቡ ወደ ቡድኑ የቀላቀለው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ግርማ ዲሳሳን ነው። ባህር ዳር ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተውና በሊጉም መልካም ጊዜያት ያሳለፈው ግርማ በሁለት ዓመት ኮንትራት ክለቡን የተቀላቀለ ሲሆን በሽመክት ጉግሳ ላይ የተንጠለጠለው የመስመር ማጥቃት ላይ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ብለው የአጥቂ አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በማራዘም የክረምት እንቅስቃሴ የጀመሩት ዐፄዎቹ በቅዱስ ጊዮርጊስ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው አምበሉ ያሬድ ባዬን ውል በሁለት ዓመት እና አይቮሪኮስታዊው ሁለገብ ከድር ኩሊባሊ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውላቸውን አራዝሟል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ