ወላይታ ድቻ አራት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የቀድሞ ተጫዋቹን ለመመለስ ተቃርቧል

በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ የሚመሩት የጦና ንቦቹ አራት አዳዲስ ወጣት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ሲደርሱ አናጋው ባደግን ለማስፈረም ተቃርበዋል።

ከወላይታ ድቻ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ከዚህ ቀደም በመሀል ተከላካይነት ሲጫወት የቆየው እና በዘንድሮው ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው መልካሙ ማቲዮስ ክለቡን የተቀላቀለ ወጣት ተጫዋች ነው፡፡ በሀምበሪቾ ከተማ ዘንድሮ በአማካይ ክፍል ሲጫወቱ የነበሩት እና ከዚህ ቀደም በድቻ ታዳጊ ቡድን ተጫውተው ያሳለፉት ፊንያስ ተመስገን እና መሳይ አገኘሁ አሳዳጊ ክለባቸውን ለማገልገል የተስማሙ ተጫዋቾች ሲሆኑ በኢኮሥኮ በዚህ ዓመት በመጫወት ያሳለፈው አጥቂው ያሬድ ዳርዘም አራተኛ አዲሱ የወላይታ ድቻ ፈራሚ ለመሆን የስማማ ተጫዋች ነው።

ክለቡ አምስተኛ አዲስ ፈራሚውን ለማግኘትም የቃል ስምምነትን ፈፅሟል፡፡ ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ ሲጫወት ቆይቶ 2009 ላይ ወደ ድሬዳዋ አምርቶ አምርቶ የነበረው የመስመር ተከላካዩ አናጋው ባደግ የ2011 የውድድር ዓመት በፕሪምየር ሊጉ ለደቡብ ፖሊስ ሲጫወት ቆይቶ ዘንድሮ ወደ መከላከያን ተቀላቅሎ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ዳግም ወደ ቀደም ክለቡ ለመመለስ ተቃርቧል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ