አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ተስማማ

ሱሌይማን መሐመድ እና በላይ ዓባይነህ ከአዳማ ከተማ ጋር ለመቀጠል ተስማምተዋል።

የቀድሞው የባንኮች እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመስመር ተከላካይ ሱሌይማን መሐመድ በአዳማ ለረዥም ዓመታት የቆየ ሲሆን ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ከተመለሰ ወዲህ በአምበልነት እያገለገለ ይገኛል። የአንጋፋው ተጫዋች ውል ለማራዘም መስማማትም ቡድኑን በወጣቶች ለመገንባት ላሰቡት አዳማዎች በልምድ ረገድ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው ውሉን ያራዘመው ባለፈው ዓመት ወደ ክለቡ የተቀላቀለው በላይ ዓባይነህ ነው። የ2007 የብሔራዊ ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪውና የቀድሞ የኢትዮጵያ መድን ፣ ወልዲያ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና መተሐራ ስኳር ተጫዋች በተሰረዘው የውድድር ዓመት ክለቡን ተቀላቅሎ ብዙም የመጫወት ዕድል ባያገኝም ውሉ ለተጨማሪ ዓመት ተራዝሞለታል።

አዳማ ከተማዎች እስካሁን ስድስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ሲስማሙ አራት ተጫዋቾችን ውል ለማደስ ከስምምነት ደርሰዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!