በወልቂጤ ውለን ለማራዘም ተስማሞቶ የነበረው ጫላ ተሺታ አሁን ደግሞ ከሲዳማ ቡና ጋር ተስማምቷል

በወልቂጤ ከተማ ከሳምንታት በፊት ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ የነበረው የመስመር አጥቂው ጫላ ተሺታ አሁን ደግሞ ለቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና ለመፈረም ተስማማ፡፡

የቀድሞው የሻሸመኔ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ከተጫወተ በኃላ ነበር 2010 ላይ ወደ ሲዳማ ቡና ተቀላቅሎ መጫወት የጀመረው። ተጫዋቹ በውሰት ለአዳማ ከተማም በመሄድ የተጫወተ ሲሆን በ2011 በሲዳማ ቤት ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ መነሻነት ዘንድሮ ወደ ወልቂጤ ሄዶ ከክለቡ ጋር መልካም የውድድር ዓመትን ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ያሳየ ሲሆን ውሉ በመጠናቀቁ ከሳምንታት በፊት በወልቂጤ ለመቀጠል ቢስማማም በድጋሚ ለቀድሞው ክለቡ ሲዳማ የሁለት ዓመት ውል ለመፈረም ተስማምቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!