ኢትዮጵያውያን በውጪ | ቢንያም በላይ በኡምአ መለያ የመጀመርያውን ግብ አስቆጥሯል

ኡምአ አቻ በተለያየበት ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ቢንያም በላይ ግብ አስቆጠረ።

በአስራ ስድስተኛው ሳምንት የስዊድን ሱፐርታን በአስራ ሥስተኛው ደረጃ የሚገኙት ኡምአዎች እና በሰባተኛው ደረጃ የሚገኙትን ብራጎች ያገናኘው ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ኢትየያዊው አማካይ ቢንያም በላይ በሃምሳ አራተኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሯል። ላለፉት ሳምንታት በወራጅ ቀጠና የቆዩት ኡምአዎች በቢንያም ጎል መሪ መሆን ቢችሉም እንግዳዎቹ ብራጎች ጨዋታው ሊጠናቀቅ አስር ደቂቃ ሲቀረው በአንድሬ ካምፕ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ አቻ በመለያየታቸው ደረጃቸው ለማሻሻል የነበራቸውን ዕድል አባክነዋል።

ከአስራ ስድስት የሊጉ ክለቦች በአስራ ሦስተኛው ደረጃ የሚገኙት ኡምአዎች በቀጣይ ሳምንት ከሜዳቸው ውጭ ዳልኩርድን ይገጥማሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!