ሎዛ አበራ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለች

በማልታው ቢርኪርካራ ክለብ ድንቅ ጊዜን ያሳለፈችው ሎዛ አበራ ትናንት ምሽት ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብላ ተመርጣለች።

የክለብ ህይወቷን በሀዋሳ ከተማ ጀምራ 2007 ላይ ወደ ደደቢት በማምራት ድንቅ ብቃቷን ያሳየችው ሎዛ አበራ ዓምና ወደ አውሮፓ በማቅናት የእግርኳስ ጉዞዋን ወደ ተሻለ ደረጃ አሸጋግራ ነበር። በደደቢት በነበረችበት ጊዜ ለ4 ተከታታይ ዓመታት የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረችው ተጫዋቿ ማልታም ከገባች በኋላ ግብ ላይ ርህራሄ ቢስ መሆኗን አሳይታለች።

ተጫዋቿ የማልታ ሊግ በኮቪድ-19 እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 30 ግቦችን አስቆጥራ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆና አጠናቃለች። በተጨማሪም ክለቧን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እንዲሳተፍ የበኩሏን አበርክታለች።

ምሽት ላይ የማልታ እግርኳስ ተጫዋቾች ማኅበር በይፋዊ ማኅበራዊ ገፁ እንዳስታወቀው ከሆነ ተጫዋቿ የ2019/20 የዓመቱ ምርጥ ሴት እግርኳስ ተጫዋች ተብላ ተመርጣለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!