ዘንድሮ በሰበታ ከተማ ያሳለፈው አጥቂ ወደ አይቮሪኮስቱ ክለብ አመራ

ብሩኪና ፋሷዊው የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋች ባኑ ዲያዋራ ሰበታ ከተማን ለቆ አሴክ ሚሞሳን ተቀላቅሏል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ዘንድሮ ሊጉ በኮሮና ቫይረስ እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ እየተጫወቱ ከነበሩ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል የ29 ዓመቱ የብሩኪና ፋሶ ዜግነት ያለው ባኑ ዲያዋራ አንዱ ነው፡፡ ይህ ተጫዋች በቤልጂየም ፈርስት አማተር ዲቪዥን ክለብ የሆነው ቱቪዝን ለቆ ነበር በመስከረም ወር ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተው ሰበታ ከተማ በአንድ ዓመት ለመቆየት በመስማማት ክለቡን መቀላቀል የቻለ ሲሆኑ በፕሪምየር ሊጉ አንድ ጎል ብቻ ቢያስቆጥርም ለጎል የሆኑ ኳሶች በማመቻቸት ረገድ ጥሩ ጊዜ አሳልፎ ነበር። ሰበታ ከሲዳማ ቡና ሲጫወት ከዳኛ ጋር ያደረገው ግብ ግብ ድርጊትም በወቅቱ ትኩረት የሳበ ጉዳይም ነበር፡፡

ባኑ የኢትዮጵያውን ክለብ ከለቀቀ በኃላ ለአይቮሪ ኮስቱ ጠንካራ ክለብ አሴክ ሚሞሳ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!