ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ አስፈረመ

የካፍ ኮንፌደሬሽን እንደሚሳተፉ ከተወሰነ በኋላ ራሳቸውን ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ ያሉት ዐፄዎቹ በረከት ደስታን አስፈርመዋል።

ከአዳማ ከተማ ወጣት ቡድን ተገኝቶ የሦስት ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቶ የነበረው በረከት ደስታ በመጨረሻም በፌደሬሽኑ በፀደቀ ውል የፋሲል ከነማ ተጫዋች ሆኗል። 

በረከት ደስታ በፋሲል ከነማ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን በፋሲል የመስመር ተጫዋቾች ላይ ያለውን አማራጭ ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!