ከፍተኛ ሊግ | ኢኮሥኮ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

በከፍተኛ ሊጉ የሚሳተፉት ኢኮሥኮዎች ዳንኤል ገብረማርያምን ዋና አሰልጣኝ አድርገው ቀጥረዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ቡድኑን ከመሩት አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ጋር የተለያዩት ኢኮሥኮዎች አዲስ የቀጠሩት አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም የዋና አሰልጣኙ ረዳት በመሆን ሲሰራ የቆየው ዳንኤል ገብረማርያምን ነው።

አዲሱ አሰልጣኝ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት የሰሩ ሲሆን በአዲሱ የወድድር ዓመት ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ሌላ ፈተና ይጀምራሉ።

ቡድኑ በ2013 ጠንክሮ ለመቅረብ የዝውውር እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ለዚህም ይረዳው ዘንድ የተጫዋቾችን የደሞዝ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ በማጠናቀቅ ወደ ተጫዋቾች ውል ማራዘም እና የዝውውር እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን የቡድን መሪው አቶ ሙልጌታ አስፋው ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!