ምዓም አናብስት ወደ ልምምድ ሊመለሱ ነው

መቐለ 70 እንደርታዎች ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል።

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ኤንዲሳተፉ ከሰሞኑ የተወሰነላቸው የ2011 የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኖቹ መቐለዎች የኮቪድ 19 የመከላከያ ፕሮቶኮልን በተከተለ መንገድ ወደ ልምምድ እንደሚመለሱ ከክለቡ ለማወቅ ተችሏል። በመስከረም 23 እና 24 ሙሉ የህክምና ምርመራዎች አድርገው መስከረም 25 ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናል።

መቐለዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው የካምፕ ሕይወት በተለየ መንገድ ዝግጅታቸው ለመጀመር እንዳቀዱም ለማወቅ ተችሏል። በዚህ መሠረትም የወረርሺኙ ሥጋትን ለመቀነስ ተጫዋቾችን በሆቴል በማሳረፍ ለቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል።

በዝውውር መስኮቱ የወሳኝ ተጫዋቾች ውል አድሰው በረከት አማረ ፣ ምንተስኖት ከበደ ፣ ሰለሞን ኃብቴ ፣ ነፃነት ገብረመድኅን እና ምንይሉ ወንድሙን ለማስፈረም የተስማሙት 70 እንደርታዎቹ በቀጣይ ቀናት የአንድ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ለማደስ በብርቱ ጥረት ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!