ከፍተኛ ሊግ | ጌዲኦ ዲላ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል

የጌዲኦ ዲላ እግር ኳስ ክለብ ለወንድ እግር ኳስ ቡድኑ ማስታወቂያን አወጣ፡፡

በተሰረዘው የ2012 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ ተፎካካሪ በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመግባት በማሰብ አሰልጣኝ ደረጀ በላይን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሮ የነበረው ጌዲኦ ዲላ አሰልጣኙን ለሀላባ ከተማ አሳልፎ ከሰጠ በኃላ ለዘንድሮው የውድድር ዘመን አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር በሁለቱም ፆታ ተሳታፊ ያደረገ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ