ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ሀላባ ከተማ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ በማለም በከፍተኛ ሊጉ ልምድ ያላቸውን አሰልጣኝ ደረጀ በላይን የቀጠረው ሀላባ ከተማ ጠንካራ የቡድን ስብስብን ይዞ ለመቅረብ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን እንዳስፈረሙ አሰልጣኙ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኙ እንደገለፁት ከሆነ በቀጣዮቹ ቀናትም አዳዲስ ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙ የገለፁ ሲሆን በክለቡ ነባር ሆነው ውላቸውን የተጠናቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾችንም ተመልክተው ውል እንደሚያራዝሙ ገልፀዋል፡፡

ሀላባ ከተማን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾች
ንጉሡ ሙሉጌታ (ግብ ጠባቂ ከጋሞ ጨንቻ)፣ ብሩክ ግርማ (ተከላካይ ከጌዲኦ ዲላ)፣ ኪሩቤል ተካ (ተከላካይ ከጌዲኦ ዲላ)፣ ሰለሞን ብሩ ተከላካይ ከጌዲዮ ዲላ)፣ ማቴዎስ ኤልያስ (የመስመር አጥቂ ከጋሞ ጨንቻ)፣ ክንዱ ባይለይ (አማካይ ከባቱ ከተማ)፣ በረከት (አማካይ ከጂንካ ከተማ)፣ ታምሩ ባልቻ (አጥቂ ከጌዲኦ ዲላ)

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!