ሎዛ አበራ ወደ ኢትዮጵያ ክለብ የሚመልሳትን ዝውውር አከናውናለች

በኢትዮጵያ የተጫዋቾች የዝውውር ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ ሎዛ አበራ በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አዲስ ክለብ መቀላቀሏ ይፏ ሆኗል።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት እና አዳማ ከተማ አጥቂ ሎዛ አበራ ባለፈው የውድድር ዓመት በማልታ ሊግ ማሳለፏ ይታወሳል። በማልታ ቆይታዋም ከክለቧ ቢርኪርካራ ጋር የቡድን እና የግል ስኬቶችን አጣጥማ ነበር። ከአንድ ዓመት የአውሮፓ ቆይታ በኋላም ወደ ሀገሯ በመመለስ የበርካታ ክለቦችን ጥያቄ ስታስተናግድ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም የሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መቀላቀሏ በአሁኑ ሰዓት ይፋ ሆኗል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሎዛ በተጨማሪ ሰናይት ቦጋለን ማስፈረሙንም በመግለጫው አስታውቋል።


ከቆይታዎች በኋላም በይፋዊ የስምምነት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሚነሱ ዝርዝሮችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!