ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከሰሞኑ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የነበረው ሀላባ ከተማ ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮቹን ውል አድሷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የሚገኘው እና ጥሩ እግር ኳስን ከሚጫወቱ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀላባ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ በመቅጠር ዝግጅቱን ከጀመረ በኃላ ከቀናት በፊት ከተለያዩ ክለቦች ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ወልዳይ ገብረሥላሴ (ተከላካይ ከጌዲኦ ዲላ)፣ ውብሸት ሥዩም (ከነቀምት አማካይ)፣ ለገሰ ዳዊት (አማካይ ከጋሞ ጨንቻ)፣ ዮሐንስ ኪሮስ (አጥቂ ከጌዲኦ ዲላ) አስፈርሟል።

እንደ አሰልጣኝ ደረጀ በላይ ገለፃ ሶስት ውላቸው የተጠናቀቁ ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝሙ ሶስት ወጣት ተጫዋቾችን ደግሞ ከታችኛው የክለቡ ቡድን እንዳሳደጉም ነግረውናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!