ዲኤስቲቪ ለቀጥታ ስርጭቱ ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው

ነገ የሚጀምረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጥታ ስርጭት ጨዋታዎቹን የሚያስተላልፈው ዲኤስቲቪ ቅድመ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።

በርከት ያሉ ቱሩፋቶችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ይዞ የመጣው የ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ነገ ታኅሣሥ 3 ቀን በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል። ይህንም ጨዋታን በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈው ሱፐርስፖርት ቅድመ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። በዚህ ዙርያ አንዳድንድ መረጃዎችን እንጠቁማችሁ።

* ጨዋታው ለመከታተል የሚፈልጉ የስፖርት ቤተሰቦች በዲኤስቲቪ ሱፐር ስፖርት ቻናል ቁጥር 229 በቀጥታ ያገኙታል።

* ጨዋታውን በቀጥታ ለማስተላለፍ የሚረዱ ሁለት የማሰራጫ ጣቢያ መኪናዎች ከኬንያ በመምጣት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገኛሉ።

* ከስድስት እስከ ስምንት ዘመናዊ ካሜራዎች በተለያዩ የስታዲየሙ ክፍሎች ጨዋታው ለማስተላለፍ የሚቀመጡ ይሆናል።

* ሱፐር ስፖርት በቀጥታ ስርጭቱ በኮሜንታተርነት እና በጨዋታ ተንታኝነት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ይጠቀማል። እነርሱም ሰዒድ ኪያር፣ ዮናስ አዘዘ፣ መኳንንት በርሄ፣ ፋሲል ረዲ፣ ሶፎንያስ እንየው፣ ግርማቸው እንየው፣ ማርቆስ ኤልያስ እና ኃይለእግዚአብሔር አድሀኖም ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ በጨዋታ ተንታኝነት የቀድሞ ተጫዋቾች አዳነ ግርማ፣ ሙሉዓለም ረጋሳ፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ) እና ግሩም ሥዩም የሚሳተፉ ይሆናሉ።

* 60 ጨዋታዎች በአጠቃላይ እንደሚተላለፉ የተገለፀው ሊጉ የትኞቹ 60 ጨዋታዎች ናቸው የሚለው ግን ሙሉ መርሐግብሩም ባይታወቅም የመጀመርያው ሳምንት ሁሉም ስድስት ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት የሚያገኙ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ