ድሬዳዋ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ብርቱካናማዎቹ ሁለት ናሚቢያዊ የውጪ ዜጋ አጥቂዎች እና ኢትዮጵያዊ አንድ አማካይ ተጫዋቾችን አስፈረመ፡፡

የናሚቢያ ዜግነት ያለው አጥቂው ኢታሞና ኪሞኔ ማረፊያው ድሬዳዋ ሆኗል፡፡ ለናሚቢያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ሲጫወት የቆየው አጥቂው 2011 ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለድሬዳዋ መጫወት የጀመረ ሲሆን የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በወልዋሎ ካሳለፈ በኃላ ዳግም የቀድሞው ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡ ሌላኛው የናሚቢያ ዜግነት ያለው ጂኒያንስ ናንጂቡም ወልዋሎን በመልቀቅ ከቡድን አጋሩ ጋር ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል፡፡

ሦስተኛው የክለቡ ፈራሚ ዳንኤል ደምሴ ነው፡፡ይህ የቀድሞው ወልዲያ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አምና በመቐለ 70 እንደርታ የነበረው አማካዩ በክረምቱ ወደ ወልዋሎ አምርቶ የነበረ ቢሆንም የክለቡን በሊጉ አለመሳተፍ ተከትሎ የምስራቁን ክለብ ተቀላቅሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ