ከፍተኛ ሊግ | ኢኮሥኮ ሁለት ተስፈኞችን ጨምሮ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ በአሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያም እየተመራ ዝግጅቱን ከጀመረ ሳምንታት ያስቆጠረው ኢኮሥኮ ከዚህ ቀደም በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ተስፈኛው አማካይ በየነ ባንጃው የክለቡ አዲሱ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከአፍሮ ፅዮን ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ ያለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ በመጫወት በአምበልነት ጭምር አገልግሏል። በ2010 በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በቅርቡ በአሰልጣኝ ተመስገን ዳናው የታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ በመጫወት ሀገሩን ከማገልገሉ ባሻገር ወሳኝ ግቦችን በማስቆጠር ከብዙሀኑ አድናቆት ተችሮታል። ታዳጊው ዘንድሮ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን ያድጋል ተብሎ ቢጠበቅም በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ተመራጭ ባለመሆኑ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ኢኮሥኮ አምርቷል፡፡

ክለቡ የመከላከያ አማካይ የሆነው ተፈራ አንለይ እና በሀዋሳ ከተማ፣ አርባምንጭ፣ ሰበታ ከተማ እና አምና በደቡብ ፖሊስ ሲጫወት የነበረው የተከላካይ አማካዩ ኤርሚያስ በላይንም አስፈርሟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ