ጋናዊው አማካይ ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቀለ

አማካዩ ካሉሻ አልሀሰን ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል፡፡

የጋናውን ክለብ ድሪምስን ለቆ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በፕሪምየር ሊጉ በነበረበት ወቅት ቡድኑን ተቀላቅሎ መልካም የውድድር ዓመትን ያሳለፈ ሲሆን ክለቡን ከለቀቀ በኃላ በኢትዮጵያ ቡና ተጫውቶ ከማሳለፍ ባሻገር መቐለ 70 እንደርታን በተሰረዘው የውድድር ዓመት አጋማሽ ተቀላቆሎ የነበረ ቢሆንም ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት እያለው የመቐለን በሊጉ ያለ መሳተፍ ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕናን ረፋዱን ተቀላቅሏል፡፡

ካሉሻ ከቢስማርክ አፒያ፣ አይዛክ ኢሴንዴ እና ሊ አንዲ በመቀጠል አራተኛው የክለቡ የውጪ ዜጋ ተጫዋች ሆኗል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ