ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሻሸመኔ ከተማ ረዳት አሰልጣኞችን ጨምሮ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ላይ ተደልድሎ የሚገኘው ሻሸመኔ ከተማ የከፍተኛ ሊጉ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሲጀመር ሀዋሳ ላይ ከቤንች ማጂ ቡና የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል፡፡ ክለቡ በቅርቡ የቀድሞው አሰልጣኙ አንዱዓለም ረድኤትን (ዴሻ) ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረ ሲሆን ረዳት አሰልጣኝ አድርጎ ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ ተጫዋች ኤፍሬም ዓአ
ለምነህን ከዚህም በተጨማሪ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂ አጥናፉ ታደሰን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል፡፡

ከአሰልጣኞቹ በተጨማሪ ክለቡ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

ተከላካዮች – ሮቤል ዳንኤል (ከጉለሌ ክ/ከተማ) ፣ ይትባረክ ሀብታሙ (ከባቱ ከተማ) ፣ ዝናቡ ዳመና (ከቡታጅራ) ፣ ክብረት ታደሰ (ከባቱ) ፣ ዳንኤል ራህመቶ (ከኤሌክትሪክ)

አማካዮች – አዲስዓለም ደሳለኝ (ከአክሱም) ፣ ሮባ ዱካሞ (ከስልጤ ወራቤ) ፣ አብዲ ሁሴን (ከስልጤ ወራቤ)

አጥቂዎች – በኃይሉ ወገኔ (ከሀላባ) እና ማናዬ ፋንቱ

ከአዳዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ ቦና ዓሊ ፣ ሮብስን በዳኔ፣ ቢኒያም ታከለ እና ሮቤል ዳንኤል ከቢ ቡድን ወደ ዋናው ያደጉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ