ከፍተኛ ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጨማሪ ተጫዋቾች አስፈረመ

በሀዋሳ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከነባሮች ጋር በማቀናጀት ዝግጅት እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ተጨማሪ ሁለት ተጫዋች አስፈርመዋል፡፡

የመሐል እና የመስመር ተከላካዩ ፋሲል ጌታቸው ክለቡን ፊርማውን አኑሯል፡፡ የቀድሞው የባህር ዳር ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ተጫዋች ለአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናው ክለብ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሌላኛው ፈራሚ ዮናስ በርታ ነው፡፡ የቀድሞው የባህርዳር ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ወልዋሎን በተሰረዘው የውድድር ዓመት አጋማሽ ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ክለቡ በፕሪምየር ሊጉ አለመሳተፉን ተከትሎ ማረፊያውን ኤሌክትሪክ አድርጓል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪኮች እስከ አሁን በድምሩ አስራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ