ወልቂጤ ከተማ ከሥራ አሰኪያጁ ጋር ተለያየ

ወልቂጤ የሥራ አስኪያጁን የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብሏል።

ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታምራት ታዬ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ለክለቡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በፃፉት እና በክለቡ ዙሪያ ላሉ አምስት አካላት ግልባጭ ባደረጉት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡

የቀድሞው ሥራ አስኪያጅ በደብዳቤያቸው እንዳሉት ክለቡ ከገጠመው ጊዚያዊ እና ግለሰባዊ ችግር አንፃር የእርሳቸው መልቀቅ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘታቸው እና የመፍትሄው አካል ለመሆን በማሰብ ለውሳኔው መድረሳቸውን አንስተዋል፡፡ በመሆኑም ግለሰቡ ከየካቲት 01 2013 ጀምሮ ሥራቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስረድተዋል፡፡ ክለቡም የአቶ ታምራትን ጥያቄ በመቀበል እንዳሰናበታቸው ማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ