ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች ይህንን ይመስላሉ።

ድሬዳዋ ከተማ አዳማን ከጨዋታ ብልጫ ጋር ከረታበት ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ፍቃዱ ደነቀን በያሬድ ዘውድነህ ብቻ በመቀየር ለዛሬው ጨዋታ ቀርቧል። አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን አዲስ አበባ ላይ የነበረው የቡድኑ ጨዋታ ተበላሽቶ የነበረ ቢሆንም በሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ጨዋታ እንደተመለሰ በመናገር ለዛሬው ጨዋታ ብዙ ለውጥ ሳያደርጉ ቀርበዋል።

ጉዳት የገጠማቸው ተስፋዬ ነጋሽ እና ሀብታሙ ሸዋለምን በስዩም ተስፋዬ እና ከቅጣት በተመለሰው አሳሪ አልመሀዲ ለመተካት የተገደዱት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ስብስቡ የገጠሙት ጉዳቶች እክል ሊሆንባቸው ቢችልም ሌሎች ተጫዋቾችም ጥሩ ቁመና ላይ የሚገኙ በመሆኑ ለጨዋታው መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ቡድኑ ከፋሲሉ ጨዋታ ባደረጋቸው ሌሎች አቡበከር ሳኒ እና ተስፋዬ መላኩ የአህመድ ሁሴን እና ሌላው በጉዳት በሌለው ፍሬው ሰለሞን ቦታ ተክተዋል። በዚህም አሳሪ እና ተስፋዬ በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካተዋል።

ጨዋታውን አባይነህ ሙላት በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
21 ፍሬዘር ካሣ
14 ያሬድ ዘውድነህ
16 ምንያምር ጴጥሮስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
11 እንዳለ ከበደ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
9 ስዩም ተስፋዬ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሤ
3 ረመዳን የሱፍ
15 ተስፋዬ መላኩ
6 አሳሪ አልመሀዲ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
8 አቡበከር ሳኒ
20 ያሬድ ታደሰ
26 ሄኖክ አየለ


© ሶከር ኢትዮጵያ