ሰበታ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በከሰዓት በኋላው ጨዋታ ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ታውቋል።

የቡድኑ ዋና ተከላካይ አማካይ ተስፋዬ አለባቸውን አለመኖር ከሀዋሳው ጨዋታ በተለየ በሌላ መንገድ ለመሸፈን እንዳሰቡ የገለፁት የሀዲያ ሆሳዕናው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተስፋዬ በቀለን በቦታው ተክተው ለጨዋታው ቀርበዋል።

በሲዳማ ከተሸነፉበት ጨዋታ አራት ተጫዋቾችን የቀየሩት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ከተጋጣሚያቸው ወቅታዊ ብቃት አንፃር ቡድኑን አብደውም ሆነ አቅልለው ላለማየት በስነ ልቦናው እንደተዘጋጁ ተናግረዋል። ባደረጓቸው ለውጦችም ዓለማየሁ ሙለታ ፣ መሳይ ጳውሎስ ፣ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ እና እስራኤል እሸቱን በመጀመሪያው አሰላለፍ ሲያካትቱ ቅጣት ላይ የሚገኘው ዳንኤል ኃይሉ ፣ ጌቱ ኃይለማርያም ፣ አብዱልባስጥ ከማል እና ፍፁም ገብረማርያም ጨዋታውን የማይጀምሩ ይሆናል።

ጨዋታውን ተካልኝ ለማ በዋና ዳኝነት ይመሩታል

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
14 ዓለምአየሁ ሙለታ
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
21 አዲሱ ተስፋዬ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
3 መስዑድ መሐመድ
9 ኢብራሂም ከድር
7 ቡልቻ ሹራ
19 እስራኤል እሸቱ

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
17 ሄኖክ አርፊጮ
25 ተስፋዬ በቀለ
14 መድኃኔ ብርሀኔ
10 አማኑኤል ጎበና
22 ቢስማርክ አፒያ
20 ሳሊፉ ፎፋና
12 ዳዋ ሆቴሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ