ድሬዳዋ ከተማ ከአንበሉ ጋር ተለያይቷል

ዘንድሮ ድሬዳዋ ከተማን በአንበልነት እየመራ ጨዋታዎችን ሲያደርግ የነበረው ኤልያስ ማሞ ከቡድኑ ጋር በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

ከ2011 አጋማሽ ከጅማ አባ ጅፋር ወደ ድሬዳዋ ያቀናው ኤልያስ ማሞ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በክለቡ መቆየቱ ይታወቃል። ከቡድኑ ጋር የሚያቆየው ቀሪ ኮንትራት ቢኖረውም አስቀድሞ በስምምነት ለመለያየት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ክለቡ ጥያቄውን ተቀብሎ በዛሬው ዕለት በስምምነት መለያየታቸው ዕርግጥ ሆኗል።

ከቡድኑ ጋር ወደ ባህር ዳር ያልተጓዘው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ባንክ፣ ቡና እና አባ ጅፋር አማካይ በአንደኛው ዙር ድሬዳዋ የሚያደርገው አንድ ቀሪ ጨዋታ ላይ እንደማይኖር የሰማን ሲሆን በቅርቡ ቀጣይ ማረፊያው ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ