ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

ከአሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን ጋር የተለያየው ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል።

የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ቡድን እና የወንዶች ቡድኑን በምክትል አሰልጣኝነት በማገልገል ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ወደ ዋና አሰልጣኝነት ከፍ ያሉት አሰልጠኝ ፍስሐ ከቡድኑ ጋር ከተለያዩ በኋላ በዛሬው ዕለት በፌዴሬሽን በመገኘት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን መቅጠሩን አረጋግጧል።

አሰልጣኝ ዘማርያም ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ እና ጅማ አባ ጅፋር ማሰልናቸው የሚታወቅ ሲሆን በተሰረዘክ የውድድር ዓመት ወልዋሎን ተረክበው እንደነበር ይታወሳል።

አሰልጣኝ ዘማርያም የወጥነት ችግር የሚስተዋልበት እና በአሁኑ ወቅት በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ውጤትን የማሻሻል ፈተናቸውን በ13ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማን በመግጠም የሚጀምሩ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ