የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ ሒደት ተጎበኘ

ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ ዘግይቶ ግንባታው እየተካሄደ የሚገኘው የብሔራዊ ስታድየም የግንባታ ሒደት ተጎብኝቷል።

ዶ/ር ሒሩት ካሣ (ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር) እና አቶ ዱቤ ጁሎ (የስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር) በተገኙበት በተገኙበት በዚህ መርሐ ግብር ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ቢሆንም ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና በግንባታው ቦታ ላይ የሰፈሩ ግለሰቦች ስራው በታቀደው ልክ እንዳይሄድ እንዳደረገው ተገልጿል ።

በቀጣይ የተጠቀሱትን ክፍተቶችን ለማረም ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የምንዛሬ ዕጥረቱን ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በመነጋገር በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ የተገለፀ ሲሆን ህገ ወጥ ሰፋሪዎችን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን እልባት ለመስጠት የመፍትሔ አቅጣጫ ተቀምጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ