ሀዲያ ሆሳዕና የተጫዋቹን ውል አድሷል

በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት የሁለገብ ተጫዋቹን ውል አድሰዋል።

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ደረጃን ይዘው የሚገኙት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ውሉ ያለቀውን መድሃኔ ብርሃኔን ውል ለተጨማሪ ዓመት ማደሳቸው ተሰምቷል። የቀድሞ የደደቢት እና ስሑል ሽረ ተጫዋች የነበረው መድሃኔ ብርሃኔ ዓምና በተሰረዘው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ሆሳዕና ከደረሰ በኋላ በሁለገብ ሚና ቡድኑን ሲያገለግል ቆይቷል።

አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለም የተጫዋቹን ግልጋሎት ለተጨማሪ ጊዜ ለማግኘት ውሉን ለአንድ ዓመት ማደሳቸው ተረጋግጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ