ሀዲያ ሆሳዕና ተከላካይ አስፈርሟል

በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ሀዲያ ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት ተከላካይ አስፈርመዋል።

በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ የሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ የሆኑት ነብሮቹ ከሰሞኑ ውል ያለቀባቸውን ተጫዋቾች ውል እያደሱ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ዓርብ የተከፈተውን የዝውውር መስኮት በመጠቀም አክሊሉ አያናውን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

የቀድሞ የሙገር ሲሚንቶ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ተጫዋች የነበረው አክሊሉ ጨደ ወልዋሎ አምርቶ የነበረ ቢሆንም በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በያዝነው የውድድር ዓመት ሳይጫወት ማሳለፉ ይታወሳል። ከሀገር ውስጥ ክለቦች በተጨማሪ ወደ የመን ተጉዞ የተጫወተው የመሐል ተከላካዩ ተጫዋቹ አክሊሉ የሊጉን ዝቅተኛ ግብ ያስተናገደውን ክለብ የኋላ መስመር አማራጭ ለማስፋት በአሰልጣኝ አሸናኒ እምነት ተጥሎበታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ