ሀዲያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ቀጣዮቹ ተጋጣሚዎች ያደራጓቸውን ለውጦች እና ተጓዳኝ ሀሳቦች እንዲህ አሰናድተንላችኋል።

በጨዋታው ከፍ ያለ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ግምታቸውን ያስቀመጡት አሸናፊ በቀለ ጅማ ላይ ድል ከተቀዳጁበት ጨዋታ ባደረጓቸው ሁለት ለውጦች በአዲስ ህንፃ ቦታ ብሩክ ቃልቦሬን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመጣ በሌላኛው ለውጥ የግራ መስመር ተከላካዩ ሱለይማን ሀሚድ በፀጋ ሰው ድማሙ ምትክ ጨዋታውን ይጀምራል።

ከተጋጣሚያቸው ጋር ተመሳሳይ አቀራረብ እንዳላቸው ያነሱት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከመልሶ ማጥቃት ይልቅ የኳስ ቁጥጥርን እንደሚያስቀድሙ ገልፀዋል። ከሲዳማው ጨዋታ ባደረጉት ለውጥ አዲስ ፈራሚዎቻቸው አስናቀ ሞገስ እና ነፃነትን ገብረመድህንን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ አምጥተው አበባየሁ አጪሶ እና ፀጋዬ ብርሀኑን አሳርፈዋል።

ፌደራል ዳኛ በፀጋው ሽብሩ ጨዋታውን በመሀል ዳኝ ለመምራት የተመደቡ አርቢትር ናቸው።

ቡድኖቹ ዛሬ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱለይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
17 ሄኖክ አርፌጮ
8 ብሩክ ቃልቦሬ
13 አልሀሰን ካሉሻ
10 አማኑኤል ጎበና
7 ዱላ ሙላቱ
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
3 አስናቀ ሞገስ
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
32 ነፃነት ገብረመድህን
27 መሳይ አገኘሁ
9 ያሬድ ዳዊት
8 እንድሪስ ሰዒድ
21 ቸርነት ጉግሳ
13 ቢኒያም ፍቅሩ


© ሶከር ኢትዮጵያ