ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ላይ እነዚህን መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው አንድ አንድ ለውጦች አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ከቅጣት የተመለሰው የግራ መስመር ተከላካያቸው አምሳሉ ጥላሁንን በሳሙኤል ዮሃንስ ምትክ የተጠቀሙ ሲሆን አሰልጣኝ ማሂር ዴቬዲስ ደግሞ ለግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽ ከመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል በመስጠት ለዓለም ብርሀኑን አሳርፈዋል።

አሰልጣኝ ስዩም ከቅርብ ተፎካካሪዎቻቸው ጋር ያሉትን ጨዋታዎች በትኩረት እንደሚያደርጉ እና የጊዮርጊስን አጨዋወት የራሳቸውንም አቀራረብ ከግምት እንደሚያስገቡ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ማሂር በበኩላቸው ሁሉም ጨዋታዎች ወሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን ከጨዋታ ሙሉ ነጥብ ለመውሰድ ያላቸውን ሁሉ እንደሚሰጡ  ጠቁመዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
6 ደስታ ደሙ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
16 የአብስራ ተስፋዬ
18 አቤል እንዳለ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ