ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በዓድዋ ድል ዕለተ በዓል የሚደረገውን የረፋድ ጨዋታ መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

ወልቂጤ ከተማ በጊዮርጊስ ከደረሰበት ሽንፈት ግብ ጠባቂው ጆርጅ ደስታን በዮሀንስ በዛብህ አቡበከር ሳኒን በበሀይሉ ተሻገር ሲለውጥ ከጉዳት የተመለሰው ሀብታሙ ሸዋለምም በተስፋዬ ነጋሽ ምትክ ጨዋታውን ይጀምራል። በኢትዮጵያ ቡና በኩል ደግሞ ከአዳማው ጨዋታ አስራት ቱንጆ ለመጀመሪያ ጊዜ በእያሱ ታምሩ የተተካ ሲሆን አማኑኤል ዮሀንስም በፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ተቀይሮ ወደ አሰላለፍ መጥቷል።

የወዳጅነት ጨዋታን ጨምሮ እስካሁን በሦስት አጋጣሚዎች የገጠሙት ቡድን እንደመሆኑ አጨዋወቱን ለመማወቅ እንደሚረዳቸው ያነሱት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቀጠል ለማሸነፍ እንደሚገቡ ተናግረዋል። የወልቂጤው አቻቸው አሰልጣኝ ደግአረገ እግዛውም የመጀመሪያ ዙሩ ጨዋታ አዝናኝ እንደነበረ አስታውሰው ዛሬም ተመሳሳይ ነገር እንደሚጠብቁ ተናግረው ለሁሉም ጨዋታዎች ከፍ ያለ ትኩረት እንደሚሰጡ ገልፀዋል።

ፌደራል ዳኛ ዮናስ ካሣሁን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት አርቢትር ሆነዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታውን ለመጀመር እነዚህን የመጀመሪያ አሰላለፎች ምርጫቸው አድርገዋል።

ወልቂጤ ከተማ

99 ዮሃንስ በዛብህ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
18 በኃይሉ ተሻገር
20 ያሬድ ታደሰ
7 አሜ መሀመድ
26 ሄኖክ አየለ

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
22 ምንተስኖት ከበደ
2 አበበ ጥላሁን
14 እያሱ ታምሩ
15 ሬድዋን ናስር
8 አማኑኤል ዮሃንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን


© ሶከር ኢትዮጵያ