አዳማ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአስራ ስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች ይዘን ቀርበናል።

ከጨዋታው በፊት ስብስቡ ባለው አቅም ቡድን ለመገንባት እየጣሩ እንደሆነ እና ሽንፈቶችን እያስመዘገበ ያለው ቡድን ለማነቃቃት የዛሬውን ጨዋታ ወሳኝ እንደሆነ የተናገሩት አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በወላይታ ዲቻ ከተረቱበት ጨዋታ ታሪክ ጌትነትን እና በቃሉ ገነነን በዳንኤል ተሾመ እና እዮብ ማቲዮስ ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል።

የባህር ዳር ቆይታቸው ከሞላ ጎደል መልካም እንደሆነ የገለፁት አሠልጣኝ ፋሲል ተጋጣሚያቸው በደረጃ ሠንጠሩዡ ግርጌ ቢገኝም ያነሰ ግምት እንደማይሰጡት ተናግረዋል። አሠልጣኙም ሀዲያን ከረታው ቋሚ ስብስባቸው አንድ ለውጥ ብቻ አድርገው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ግርማ ዲሳሳን በሳለአምላክ ተገኘ ለውጠዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን በዋና ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

አዳማ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
13 ታፈሰ ሰርካ
28 አሚኑ ነስሩ
22 ደሳለኝ ደባሽ
5 ጀሚል ያዕቆብ
6 እዮብ ማቲያስ
26 ኤልያስ አህመድ
25 ኤልያስ ማሞ
9 በላይ አባይነህ
32 ያሬድ ብርሀኑ
10 አብዲሳ ጀማል

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪሰን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
8 ሳምሶን ጥላሁን
18 ሳለአምላክ ተገኘ
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
9 ባዬ ገዛኸኝ


© ሶከር ኢትዮጵያ